1.
ፍጹም መሆንን እወዳለሁ የሱስ
ለዘላለም በውስጤ እንድትኖር
ጣዖትን ስበር ጠላትን አርቀው
እጠበኝ ከበረዶ እነፃለሁ
እነፃለሁ ከበረድ ይልቅ
እጠበኝ ከበረዶ እነፃለሁ
2.
ኦ ጌታ ከዙፋንህ ተመልከተኝ ፍጹም መስዋዕትን ለማቅረብ እርዳኝ
ያለኝን ሁሉ ላንተ እሰጣለሁ
እጠበኝ ከበረዶ እነፃለሁ
3.
በትህትና ልኑር ጌታ የሱስ
ከእግርህ በታች ሆኜ ላመስግንህ
የፈሰሰውን ደምህን እንዳስታውስ
እጠደኝ ከበረዶ እነፃለሁ
4.
በትእግሥት ስጠብቅህ ጌታ የሱስ አሁን ና አዲሱን ልብ ፍጠርልኝ
ለፈለገህ ሁሉ እምቢ አትልም
እጠበኝ ከበረዶ እነፃለሁ