ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #151h / Song #151h

ስሙ የሱስ ሲጠራችሁ

Hark! The Voice of Jesus Calling

ምድብ / Category: ሥራ / work
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ስሙ የሱስ ሲጠራችሁ ማንን ልዘዝ ሲላችሁ መከሩ ደረሰላችሁ
ማን ይከውን ነዶውን
የሱስ በጩኸት ይጠራል
ዋጋችሁን ይሰጣል
ማን በደስታ ይመልሳል ጌታ ሆይ እኔን ላክ ሲል
2.
ባሕሩን ባትሻገሩ
አሕዛብም ቢርቋችሁ
ካላችሁበቱ ሥሩ
ከበሩ ሳትርቁ
የመልአክ ያክል ባትሠሩ
እንደ ጳውሎስ ባትሰብኩ
የየሱስን ፍቅር አውሩ
እርሱ ሞተልኝ በሉ
3.
ጠባቆችም ባትሆኑ
በጽዮን ግምብ ሁናችሁ
አሳዩ የሰማይ መንገድ
ሁሉም በዚያች እንዲሔድ
በጸሎትም ደግፏቸው
ወደ ሰማይ ምሯቸው
እንደ ታመነውም አሮን
ደግፉ ሰባኮችን
4.
ነፍስ ሁሉ ሲጠብቃችሁ
የሱስም ሲጠራችሁ
በስንፍና ሁላችንም
አንበል ሥራ የለም
በደስታ ሥራውን ሥሩ
አቤት እነሆኝ በሉ
በርሱ ሥራም ስትጠሩ
እነሆኝ ላከኝ በሉ
100%
100%