1.
ቀርቧል ሌሊቱ ሥሩ ማልዳችሁ ተነሡ
ጤዛው ሣይረግፍ ሥሩ ባበቦች ዙሪያ
ቀኑ እንዳይሄድባችሁ ብርሃን ሣል ሥሩ
ቀርቧል ሌሊቱ ሥሩ ሥራ ሊፈጸም
2.
ቀርቧል ሌሊቱ ሥሩ ቀትር ሣል ሥሩ
ጊዜያችሁን አታጥፉ ልታገኙ ዕረፍት
እያንዳንዷን ደቂቃ ተግታችሁ ሥሩባት
ሌሊቱ ቀርቧል ሥሩ ሥራ ሊፈጸም
3.
ቀርቧል ሌሊቱ ሥሩ የተተነበየው
በብርሃን ጊዜ ሥሩ ሊያልፍ ነው ቀኑ
እስከ መጨረሻ ሥሩ ጊዜ አለላችሁ
ጨለማ ሣይሆን ሥሩ ሥራችሁ ሳይቆም