ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #208h / Song #208h

የሱስ ሕዝቦችን የጠራቸው ዕለት

When Jesus Shall Gather the Nations

ምድብ / Category: ፍርድ / Judgement
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የሱስ ሕዝቦቹን የጠራቸው ዕለት
በጉባዔው የቀረቡ ዕለት
በፍርዱ እንዴት እንቆማለን
ፍርድ ሊሰጠን የጠራን ዕለት
ስንዴን በጐተራ ያጠራቅማል
ገለባን ግን በእሳት ያነዳል
እንዴት በፍርዱ እንቆማለን
በትልቁ የትንሣኤ ቀን
2.
የመድኃኒታችን ቃል እንስማ
መልካም ባሪያ የታመንህ ሲል
ፍርሃትም እንዳያንቀጠቅጠን
ከ ዙፋኑም እንዳንጠፋ
3.
ልጆቹን ሲያያቸው ይደሰታል
ማኅተሙን በተዋጁት ያያል
የሰማይ ግርማ ያለብሳቸዋል
ትሁታንም ያደርጋቸዋል
4.
እንግዲህ በንቃት እንጠብቀው
መብራታችንንም አብርተን
ሙሽራው ለሠርግ የጠራን ዕለት
ደስ ይበለን በዚያችው ዕለት
5.
ጸንተን እንመልከት ወደ ሰማይ
በትዕግስት ጊዜውን እንጠብቅ
ጉዟችንን ከዚህ ስንጨርስ
በጌትነቱ ደስ ይለናል
100%
100%