1.
የምድር ኃብት ወይም ወርቅ
ምን ያደርግልኛል
ከሰማያዊ ቤቴ
ከመንጋው እሆናለሁ
በሰማያዊ መዝገብ
ከመጻሕፍቱ ውስጥ
ንገረኝ መድኃኒቴ
ስሜ ተጽፏል ወይ
ተጽፏል ወይ ስሜ
በሰማዩ መዝገብ
ስሜ ተጽፎአል ወይ
ተጽፏል ወይ ስሜ
2.
ጌታ ሆይ የኔ ኃጢዓት
እንዳሸዋ በዛ
ግን የአምላካችን ደም
በቂዬ ነውና
ተስፋ ከሚያበራ
መዝገብ ተጽፎአል
ኃጢዓቴ ቢቀላ
እንደ በረድ ነፃ
3.
የምታምር ከተማ
የብርሃን ቤት ያላት
ንጹህ ልብስ የለበሱ
ቅዱሳን ያሉባት
መልካሙን የሚያበላሽ
ክፉም አይገባባት
መልአክ የሚጠብቃት
ስሜ ተጽፏል ወይ