1.
ይህ ዓለም የአብ ነው
ጆሮዬም ሲሰማ
ይዘምራል ፍጥረት ሁሉ
የሰማይን ዜማ
ይህ ዓለም የአብ ነው
ያረካል አሣቤን
ቋጥኝ ዛፍን ሰማይ ባህርን
እጁ ሰራ ሁሉን
2.
ይህ ዓለም የአብ ነው
ወፎች ሲዘምሩ
የጧት ጮራ እየበራ
ላምላክ መሰከሩ
ይህ ዓለም የአብ ነው
በሁሉም ያበራል
በለም ለም ሣር ይታየኛል
የትም የት ይገኛል
3.
ይህ ዓለም የአብ ነው
ከቶ አትፍራ ነፍሴ
ምንም ኃጢአት ቢበረታ
አምላክ ነው ንጉሤ
ይህ ዓለም የአብ ነው
ልቤም አይቸገር
አምላክ ነግሷል ሰማይ ዘምር
ደስ ይበልሽ ምድር