1.
ያምላክን ኃይል ልዘምረው
ጋራ የሠራውን
ባሕርን የዘረጋውን
ሰማይ ያረጋውን
ፀሐይ በቀን ያወጣውን
በሌትም ጨረቃን
ከዋክብት ጨረቃም ደግሞ
ያከብራሉ ቃሉን
2.
ደግነቱን ልዘምረው
ምድርን ያረካውን
ዓለምን በቃሉ ፈጥሮ
መልካም አለ ሁሉን
ዓይኔን ባዞርሁበት ሁሉ
ድንቁ ተገለጠ
ሰማይ ሆነ ወይም ምድር
ሁሉም ክብር ሰጠ
3.
ፍቅርህን የማያስታውቅ
አንድም ፍጥረት የለም
ሁሉ አንተን ይታዘዛል
ደመና ነፋስም
ለፈጠርኸው ፍጥረት ሁሉ
የምትሰጥ ምግብን
አንተ የማትገኝበት
አንድም ቦታ የለም