ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #183t / Song #183t

ለእኔም አባቴ ሆይ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
መዋረዳቸውን አይተህ አንተ ባርከሃቸው
የቤትህን ልጆች አንተ ሰብረሃቸው
ትዕቢታቸው ቀርቶ በትሁት ልባቸው
እንባቸውን ሲያፈሱት ለአንተ አየኋቸው
ለእኔም አባቴ ሆይ ልቤን ስበርልኝ
እኔነቴ ቅርቶ ጸጋህ እንዲበዛልኝ
ትዕቢቴን ሽረህ ትህትና አልብሰኝ (2x)
2.
ጌታ ዘወትር መሰበርን ሽቼ
አብዝቼ እጮሃለሁ ሌተቀን ተግቼ
እስከመቸ ድረስ ሕይወቴ እንዲህ ደርቆ
እኖራለሁ ጌታ ልምላሜ አርጐ
3.
የመሰበር ፍላጐቴ ግለቱ ሳይበርድ
ሰማዬችን ከፍተህ ምነው ብትወርድ
ምርኩዜን ፈትነህ እባክህ ስበረኝ
ትሁትና ታዛዥ መሆን አስተምረኝ
4.
የራሴን ማንነት ያኔ በርግጥ እረዳለሁ
የውስጥ ዓይኔ በርቶ አብዝቼም አያለሁ
በፍፁም ግልጽነት ስምህን አውጃለሁ
በበረከት ሙላት አስከብርሃለሁ
100%
100%