ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #165t / Song #165t

መነቀፍን ፈርቶ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
መነቀፍን ፈርቶ ማመን አፍሮ
ውድ አምላኩን ትቶ ቃልኪዳኑን ሰብሮ
ኧረ ስንቱ ስንቱ ሰመጠ ባሕር ገብቶ
ጌታ ቶሎ ድረስ እርዳኝ ብሎ እጁን ዘርግቶ ተጸጽቶ
1.
በመንፈስ ጀምሮ ሮጦ ሮጦ
ከዓለም ማዕረግ መስቀል መርጦ
ዛሬ ግን በወሬ ልቡ ቀልጦ
መመካከር ያዘ ጠላት መርጦ
2.
እርግማን አይደለም መቃለሉ
መነቀፍ ክብር ነው አስተውሉ
ከአሁኑ ዓለም ተወዳጅቶ
ክርስቶስን መተው ይቅር ከቶ
3.
መስቀሉን ከጫንቃቸው ለጣሉ
እኛም ክርስቲያኖች ነን ለሚሉ
ይለፍ ለሌላቸው መንገደኞች
እንጸልይላቸው ለኮብላዮች
4.
መስጠሙን ቢረዳ ዓይኑ በርቶ
ንስሃ ቢገባ ዳግም ቀንቶ
እጅህ መቼ አጠረ የማዳንህ
ከጥልቁ ቢጣራ ድኩም ልጅህ
100%
100%