1.
ያምላክ ወገኖች ለሠልፉ ውጡ አምላክ ሲዋጋ እንድታዩ
ጠብቁ ቁሙ ማዳኑን እዩ
በርሱ ማሸነፍ እንድረኩ
ንቁ ቁሙ ያምላክ ወታደሮች
ቃሉን ያዙ ለሁሉ አዳርሱ
አሁን ሂዱ ሃሌ ሉያ በሉ
የሠልፉ መሪ ጌታ አምላክ ነው
2.
2.ታላቅ አምላክ ሆይ
ስንጠራህ ስማን
አሁን ደግፈን በጸጋህ
ጦርነት አልፎ ድልህ ሲታወጅ
በፊትህ ቀርበን እንድናይህ
3.
በሃይልህ ታጥቀን እንጓዛለን
አንተ ስትመራን አንፈራም
ቃልህ ለእግራችን መብራት ነውና
አንተን ታምነን ከቶ አንወድቅም
4.
በርቱ እላንት ሰዎች
ባንድ ላይ ስንኖር
አብረን እየዘመርን
የድል መዝሙርን
ክብርና ምስጋና ለንጉሣችን
ለዘልዓለም በደስታ
እንዘምራለን