ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #150t / Song #150t

ለእኔም ያንን ፀጋ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የመከራ እቶን የማንጠሪያ እሳት
የመፈተኛ ፍም የመመዘኛ ጣት
ነበር በጀግኖች ዘንድ ባለፉት ጦረኞች
ባለፉበት መንገድ የድል ባለቤቶች
ለእኔም ያንን ፀጋ በሕይወቴ አምቄ
በችግሬ ሰዓት ጌታዬን ጠብቄ
ልደርስ እወዳለሁ ወደዚያ ደረጃ
በሚሰጠኝ ጉልበት በእምነት እርምጃ
2.
በቀደመው ትውልድ እሳት ነበር ልኩ
ለእምነት ትጋዳዮች የትግል መድረኩ
ለማይጠፋው ክብር ለሕያውም ተስፋ
ተዋግተው አልፈዋል በትልቅ ነቀፋ
3.
አምላካቸው ከብሯል በአምልኮ ስግደት
በትልቅ ተጋድሎ በወንጌል ጤንነት
ከብረው አስከብረው የሕይወታቸውን ጌታ
ሊገናኙት ወጡ ያንን ባለ ውለታ
4.
እኛም ተጠርተናል እንምሰል እነርሱን
የመከራን እሳት እንድናየው ልኩን
ስለዚህ ተጋደል የወንጌል አርበኛ
ሠይጣንን ግጠመው ያንተን ወደረኛ
ነው-ና- ድል የእኛ
100%
100%