ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #195t / Song #195t

እታገላለሁ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እታገላለሁ እታገላለሁ
እስከ መጨረሻው እታገላለሁ
የእስራኤል አምላክ ድል እንደሚሰጠኝ እምናለሁ
1.
ጉልበቴን አጠንክሬ ክንዶቼን አበርትቼ
እጓዛለሁ በደስታ ሳይከፋኝ ተፅናንቼ
2.
የሰላምን ወንጌል በእግሬ ተጫምቼ
በክንፉ ተማምኜ በደሙም ተሸፍኜ
3.
ፍላጻ የማይበሳውን ጥሩሩን እልብሳለሁ
ሕይወቴን ላላስድፍር በተጠንቀቅ ቆማለሁ
4.
እምነት ጋሻቸው ሆኖ ቅዱሳን ከተጓዙ
ኑሯቸው ከተቃና ድልን ከተቀዳጁ
5.
በመታገል ከሆነ ማሸነፍ ድል መንሳት
ከዚህ ዓለም ገዢ ጋራ ከክፋትም ሠራዊት
6.
የተዘጋጀልኝን ከኢየሱስ ከጌታዬ
እወስዳለሁ አክሊሌን በሚገባ ታግዬ
100%
100%