ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #119t / Song #119t

አቤቱ መባረክን ባርከን

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ
1.
ያቤጽንም ሰምተሃል እንደዚህ ሲለምንህ ነፍሱን ባርከህለታል አገሩንም አስፍተህ
2.
በልጅህ ስቃይና በጣር የተወለድን እኛም ፍሬዎችህ ነን አስባስበህ ጠብቀን
3.
ከፊትህ አትጣለን እንማጸንሃለን በሞገስህ አስበን በምህረትህ ጐብኘን
4.
ሰማያቱም ይከፈቱ መንፈስህ ይፍሰስልን ሕይወታችን ትረስርስ ነፍሳችን ትጥገብልን
5.
ብቻችንን አንቅር አብዛን እየባረክህ አበልጽገን በፀጋህ ታደገን በቃልህ
6.
እግዚአብሔርን በማወቅ ምድር እስክትሞላ ምልጃችን ይቀጥላል ጉልበታችን ሳይላላ
100%
100%