ኢየሱስን እንደ ሰው አትጠራጠረው
መዋሸት አያውቅም ተስፋህን ጠብቀው
አይጥልህምና በመከራ ጥራው
አፍህ አያመነው በልብህ አትግታው
1.
ከጠላት ፍላፃ ከሰይፍ ያድንሃል
በረህብም ዘመን ከሞት ያስጥልሃል
ስሙን ያስከብራል ቁም ነገርን ያውቃል
ሕጻን ስላይደለ ያለውን ይፈጽማል
2.
በታማንነቱ ተው ገደብ አትስጠው
ለወላዋይነትህ ፅናት አትንፈገው
የዘለዓለም አምላክ እግዚአብሔር አይዋሽም
የገባልህን ቃል ፈፅሞ አይክድም
3.
ከእርሱ ጋር እስከሆንክ ከአንተ ጋራ ነው
አውጥቶ እንዳይጥልህ ብቻ አትተወው
አስብ ቆም ብለህ ያሳለፍከውን ዘመን
ዛሬም አምነህ ጥራ ያኔ ያዳነህን
4.
ስሙን እየጠራህ ስንቱን አምልጠሃል
ከስንቱስ አደጋ ስንት ጊዜ ድነሃል
ውለታውን ሲረሱ ጌታ ቅር ይለዋል
በቃሉ ብታምን ሁሉ ይቻልሃል