1.
ተስፋህ ጨልሞ ጭንቀት አስጥሞህ
መጥፋትህ ታይቶኝ ከዚያ ጣር አወጥቼህ
ደስ ብሎህ ነበር አግኝተህ እፎይታ
ለምን ነው ዛሬስ የሆንከው ከርታታ
2.
በእኔ ተማምነህ ስትመላለስ
በእንባ በፀሎት ቀርበህ ስትታደስ
የነበረህ ወዝ መልክህስ የታለ
ናና ታረቀኝ ፀጋዬ እያለ
3.
የፍቅር ወንጌል ለሌላው ሰብከህ
ሸክማቸው ከብዶህ ለጠፉት አልቅሰህ
መስክረህ ወደ ሕይወት አምጥተህ
ሳይህ አዝናለሁ አንተ ግን ኮብልለህ
4.
ቤቴ ናፍቆህ ብትመለስልኝ
ይቅርታ ፈልገህ ብትመጣልኝ
የምህረት እጄስ ተዘርግታለች
የፍቅር እንባም ዓይኔ ታፈሳለች