ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #98t / Song #98t

ቃሉን ከቶ የማያጥፍ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ቃሉን ከቶ የማያጥፍ
ታማኝ አምላክ ነውና
የነገረንን ሁሉ ፈጽሞት አይተናልና
ከፍ ከፍ እናደርገዋለን በምሥጋና
1.
የኃጢአትን ከተማ የዲያብሎስን ሥራ
ሲያፈራርሰው አይተናል ያን ምሽግ ያንን ተራራ
ጌታችን ኢየሱስ ተገልጦ የሕይወታችን ብርሃን
የተስፋ ቃሉን ፈጸመው በሞቱ እኛን በማዳን
2.
በሰላምና በሕይወት በበጐ ነገርም ምክር
አበሳችን እንዲወገድ እሮሮአችንም እንዲቀር
በእኛ ያለውን ነገር ጌታ እግዚአብሔር አይቶ
ቀንበራችንን ሰበረው ለቅሶአችንን እርሱ ሰምቶ
3.
የሲኦልን ማስፈራራት የመከራን አውሎ ነፋስ
የኃያላኑን ጭካኔ የቁጣቸውን እስትንፋስ
የማዕበሉን ሁሉ ጩኸት የዓመጽንም ዝማሬ
በሥልጣኑ ቃል ገስጾ ዝም አሰኝቶታል ዛሬ
4.
የመማጸኛ ግንብ ነው የድሆች ሁሉ መጠጊያ
ምቹ መሸሸጊያ ዓለት የለንም ከኢየሱስ ወዲያ
ብዙዎቹም ይድናሉ ገብተው ከዚህ መጠለያ
ስለሚሆንልን ሁሉ ይክበር ጌታ ሃሌሉያ!
100%
100%