ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #120t / Song #120t

በእምነት ድል እየነሱ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በእምነት ድል እየነሱ ያለፉትን
የቀደሙትን እያየን ከፊታችን
ልንቆም ያስፈልገናል ለጌታችን
የሕይወት ምርጫችን
እርሱ ነውና ዋስትናችን (2x)
1.
ከሁሉ የሚበልጠውን ተመልክተው
ከየምድሩ ጉድጓድ ተቅበዝብዘው
ነፍስን ከሚዋጋ ምኞት ርቀው
ወንዙን ተሻገሩ አሸንፈው (3x)
2.
ቅን ከምትመስል ሰፊ መንገድ
ወጥተን በጠባቡ ስንሰደድ
በዚህ ጐዳና ላይ ሕይወት አለ
ቆርጦ ለሚከተል የታደለ (3x)
3.
ባለ ፀጋ ሲሆን ደህይቶልን
ባለ ማዕረግ ሲሆን ተዋርዶልን
እውነተኛውን ፍቅር ገለጸልን
እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን (3x)
100%
100%