ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #84 / Song #84

በኃይሉ ችሎት በርቱ ወገኖች

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እጅ እንዳትሰጡ የእግዚአብሔር ምርጦች
የፅድቅ ዕቃ ጦር ይዘን ዘምተናል
የጠላት ምሽግ በእምነት ንደናል
ጠላት ሲሸበር ሲያፍር አይተናል
ባንተ ኢየሱስ ድል አድርገናል
ባንተ ኢየሱስ ድል አግኝተናል
1.
ወገባችሁን በፅድቅ በእምነት ታጠቁና
የፅድቁንም ጥሩር በደንብ ልበሱና
በሰላሙ ወንጌል እግራችሁ ተጫምተው
በጌታ በኢየሱስ ተነሱ እንግጠመው
2.
የመዳን ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ
ታጥቀን እንነሳ በፀሎት እንክነፍ
ፀሎት የማይሰራው በምድር የለምና
ጠላትን ግጠሙት ውጡ በምስጋና
3.
በሚንበለበሉት የጠላት ፍላፃ
ተወግቶ ሳይቆስል ማንም ሳይጐዳ
ፍላፃው ይከሽፋል የእምነት ጋሻ አንሱ
በየሱስ አይተናል ምሽጐች ሲፈርሱ
4.
ውጊያችን ከሥጋ ከደም ጋር አይደለም
ከዲያብሎስ ጋር ነው እኛ ምንፋለም
ስለዚህ ወገኔ ከኃጢያት ተጠበቅ
የቆመ ሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ
100%
100%