ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #116d / Song #116d

በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይሆናል

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: እንድሪያስ ሐዋዝ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
እጅግ እየጮኸ ማዕበሉ ሲነሣ
ታንኳችንን ሊጥል ሊያሰምጠው ሲመጣ
የማዕበሉ ጌታ የሱስ ከኛ ጋር ነው
ሰላም ይሞላናል የሱስ ጸጥ በል ሲለው።
በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይሆናል
ባሕሩን ደግሞ ከፍሎ ያሻግራል
ይሄ እግዚአብሔር እንዴት ድንቅ ነው
እንዴት ልዩ ነው
ሌላ (3) ምን ይባላል እግዚአብሔር ይመስገን።
2.
ጨለማ በርትቶ ዓይናችንን ሲወጋ
ጠላት ጦሩን ሲያስግዝ ምሽግን ሊያናጋ
የጨለማው ሥልጣን ኃይሉ ተገፈፈ
ብርሃን ይሁን ያለው የሱስ አሸነፈ።
3.
መሻገር ባሕር ውኃ ሞልቶ
ልባችን ሲወድቅ በፍርሐት ተውጦ
ባሕሩን ከፈለው እኛም ተሻገርን
ልዩ ነው ኢየሱስ ስሙ።
4.
እስቲ በምስጋና ስሙን እናክብረው
ይህን ድንቅ ኢየሱስ ሌላ ምን እናድርገው
ሃሌ ሃሌ ሉያ እግዚአብሔር ይመስገን
ስሙ ድንቅ ነውና ይኸው ምስጋናችን
100%
100%