ለዛሬ አበቃኝ ጠብቆ
ከጐኔ ሆኖ ደግፎ
ለዚህ ሁሉ እኔ የምለው
የለኝ ሌላ ተመስገን ነው
1.
ፍቅሩ ለእኔ ልዩ ነው
የሚያስብልኝ በጐ ነው
ፍፃሜ ሁሉ ያማረ ነው
ህይወት አብዝቶ ለመስጠት ነው /2/
2.
ሳሳዝነው እኔን ታግሶ
ስበድለውም ይቅር ብሎ
በህይወት ያቆመኝ ጌታ
እኔም ላክብረው በደስታ/2/
3.
እርቄ እንዳልሄድ ከፊቱ
እንዳልኮበልል ከቤቱ
በቸርነቱ ደግፎኝ
በቤቱ ይኸው አቆመኝ /2/
4.
የተጣልኩትን አንስቶኝ
እናትና አባት ሆነልኝ
ሰው ሆኜ ዛሬ ቆሜአለሁ
ስለዚህ አከብረዋለሁ /2/
5.
ከጥፋትና ከአደጋ
ከሀዘንና ከመከራ
ከሁሉ ነገር ታድጐ
ለዛሬ አበቃኝ ተጠንቅቆ /2/