በኃጢአታችን ሙታን ሣለን
ምህረትህ እጅግ የበዛልን
ዛሬም በፊትህ ተንበርክከን
እንልሃለን
ጌታ አንተ ባርከን
የሱስ አንተ ባርከን
ጌታ አንተ ጐብኘን
የሱስ አንተ ጐብኘን
1.
እንደሥራችን ያልከፈልከን
እናንት ደካሞች ኑ ብለኸን
ቆመናል ጌታ ተቀበለን
ዝም አትበለን
2.
አንተ አባታችን ሆነኸናል
እኛም ልጆችህ ተብለናል
ሁሌም ክንድህ ያስፈልገናል
ይኸው ቀርበናል
3.
ዛሬም ወደ ቤትህ መጥተናል
ፈውስ ከአንተ ዘንድ ፈልገናል
በሥጋም ይሁን በመንፈስ
እንድንታደስ