ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #160d / Song #160d

ድንቅ ነው ለእኔ ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ታምራት ኃይሌ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ድንቅ ነው ለእኔ ጌታ
ድንቅ ነው ለእኔ ኢየሱስ
ሞኝነት ቢመስላት ለዓለም
ድንቅ ነው ለእኔ ዘለዓለም 2X
1.
አሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሰኝ ኖሬ
ሠላሳ ስምንት ዓመት እግሮቼን ታስሬ
ዛሬ ተፈወስኩኝ ቀሚሱን ዳስሼ
ይኸው እዘላለሁ በሥሙ ታድሼ
2.
ግንበኞች የናቁት የማዕዘን እራስ
ለእኔ ግን ድንቅ ነው ውዴ ጌታ ኢየሱስ
ብዙዎች ያጥላሉታል ርካሽ ዕቃ አድርገው
ለእኔ ለደካማው ኢየሱስ ድንቅ ነው
3.
ሞኝ ነህ ይሉኛል ሳይረዱት ቀምሰው
ተመለስ ይሉኛል ዋጋ ቢስ አደርገው
አልፈልግም ካልኩኝ ጭቅጭቅ ምንድነው?
እንቢ አሻፈረኝ ኢየሱስ ድንቅ ነው
4.
ገንዘብም ውድ ነው ውበትም ድንቅ ነው
ለእኔ ኢየሱስ እንጂ ይህ ሁሉ ከንቱ ነው
እጅህ ምሥኪን ድሃ ታናሽ ሰው እመስላለሁ
ዕጹብ ድንቅ ውድ ዕቃ ኢየሱስን ይዣለሁ
100%
100%