ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #171 / Song #171

የእግዚአብሔርን ጥልቁን ሚስጢር

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የእግዚአብሔርን ጥልቁን ሚስጢር
ትችላለህ ወይ? ልትመረምር
ከሰማይም የራቀውን ከስዖልም የጠለቀውን
ምን ልታደርግ ትችላለህ? x2
1.
ወሰን የሌለውን አምላካችንን
ጠባይን ወይም ሥራዎቹን
ማንም ሊያታለው አይችልም
በመመራመር አይደረስም
2.
ቅዱስ አምላካችን በሚስጢር
ባስፈሪ ግርማ የሚኖር
ብዙ በመማር የታመኑ ሰዎች
አላገኙትም ጥበበኞች
3.
በብዙ ጥበብ በብዙ ዕውቀት
እጅግ ብርቱ ሆነው በዓለም ላይ ያሉት
ጨረቃ ላይ ደርሰው አላገኙትም
በሰማይ ላይ በረው አላገኙትም
4.
ደመነና ጭጋግ በዙሪያው ነው
ጽድቅና ፍርድም በዙፋኑ ነው
በጠባብ አእምሮ አይገመትም
ርቀው በመሄድም አይደረስም
5.
ሰው በሰራው ዕቃ ሊፈልጉት ወጥተው
አንድ ኃይል እንዳለ አምነው ተመለሱ
እኛ ምናመልከው ያንኑ ኃይል ነው
እስከመጨረሻም የምንተከለው
100%
100%