1.
አንድ ጊዜ አይደለም ሁለት ጊዜ
ጌታ የመከረኝ በግሳጼ
እንደ እኔማ ቢሆን እንደ ሀጢያቴ
የቁጣ ልጅ ነበርኩ ከፍጥረቴ
ዛሬ ግን መክሮኝ ሰዉ ሆኛለሁ
በመቅደሱ ዉስጥ አዜማለሁ
ወደ መቅደሱ ስገባ
ድምጼን ላሰማ በምስጋና
በፍቅሩ ስቦ የመከረኝን
ባማረ ስፍራ ያስቀመጠኝን
ከፍ ላድርገዉ እግዚአብሔርን
2.
አሁን ዞር ብዬ ከኅላ ሳየዉ
መራራዉ ህይወቴ ዛሬ የጣፈጠዉ
እንዴት ያለዉን ሰዉን ለወጥከዉ
አምላኬ እግዚአብሄር ስራህ ድንቅ ነዉ
ገመድ ባማረ ስፍራ ወድቃልኝ
ባምላኬ ርስቴ ተዋበችልኝ
3.
አንካሳ ነበረኩ መሄድ የማልችል
እውርም ነበርኩ ማየት የማልችል
የሱስ የሚባል አንድ ወዳጅ አይቶኝ
በእጆቹ ዳሶኝ በድንቅ ፈወሰኝ
እንደርሱ ያለ የለኝምና
ዛሬም ቆሜያለሁ በምስጋና