ጠፊዋን ፡ ዓለም ፡ ተለይቼ
ለዘለዓለም ፡ ተሰናብቼ
የሚሞተው ፡ ተለውጦ
የማይሞተውን ፡ ኢየሱስን ፡ ለብሶ (2x)
1.
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ልኖር ፡ እናፍቃለሁ
ዓለምንና ፡ ሃሳቧን ፡ ትቻለሁ
ከላይ ፡ የሚመጣውን ፡ እጠብቃለሁ
በቅጽበት ፡ ወደእርሱ ፡ እነጠቃለሁ
2.
በጉጉት ፡ ናፍቆት ፡ ፊቱን ፡ ሳይ
ኢየሱስን ፡ ሳገኝ ፡ በላይ ፡ በሰማይ
ፊቱን ፡ ስመለከት ፡ እምባዬን ፡ ሲያይ
እየዳሰሰ ፡ ዓይኔን ፡ ያብሳል
3.
ጌታ ፡ መምጣቱ ፡ ያሳውጃል
በደጅ ፡ እንደቆመ ፡ ሕይወቴም ፡ ያውቃል
ቀኑ ፡ እንደደረሰ ፡ ተረድጄ
ተጨማሪ ፡ ዘይት ፡ ልግዛ ፡ ተግቼ