በምህረትህ በሕይወት ላቆየኸኝ
በፊትህ እንድገኝ ለረዳኸኝ
ምስጋና ምስጋና ይኸው አለኝ
1.
ፀሎቴን በጊዜው ፈጥነህ ለምትመልስ
ቸርነትህን ለኔ ለልጅህ ምትለግስ
በመውጣት መግባት ለምትጠብቀኝ
ምስጋና /3/ ነው ያለኝ
2.
የማታሳፍረኝ ዘውትር በጠላት ፊት
ከጐኔ እየሆንክ ለምትሰጠኝ እምነት
በፍቅር ክንፎችህ ቅጥር ለሆንክልኝ
ምስጋና /3/ ነው ያለኝ
3.
ከውጣ ውረድ ውስጥ ሁሌም ላወጣኸኝ
ከጥፋት ጐደና ከሞት ለታደግከኝ
በልጅህ ስቃይ ሞት ሞቴን ለሻርክልኝ
ምስጋና /3/ ነው ያለኝ
4.
በድካሜ ሁሌም ሀይልህ ይገለፃል
በቤትህ እንድኖር ፀጋህ አግዞኛል
እንዳገለግልህ ለምትደግፈኝ
ምስጋና /3/ ነው ያለኝ