1.
አሁን አያለሁ ባሕሩን
የጠለቀ ምንጩን
ኃያል መድኃኒቴ የሱስ
ያሣየኛል ቁስሉን
የሚያነፃውን ምንጭ አየሁ
ከዚያም በመጥለሜ ነፃሁ
ምስጋና ይሁን ላነፃኝ
አነፃኝ በጣም አነፃኝ
2.
አዲስ ፍጥረት ይፈጠራል
ደሙም ይናገራል
የኃጢዓት ሥጋ ይሞታል
በሚያነፃው ደም ኃይል
3.
ልራመድ በሰማይ ብርሃን
ከኃጢዓትም በላይ
አንጽቼ ልብስ እና ልቤን
ክርስቶስ በኔ ይንገሥ
4.
ፀጋውም አስገራሚ ነው
ደሙን አፈሰሰ
የሱስን ብቻ ማወቅ ነው
ለኔ ተሰቀለ