1.
በደም የመላ ምንጭ አለ
ተቀዳ ከክርስቶስ
ከዚያም የታጠቡ ኃጥአን
ከበደል ሊነፁ
ከበደል ሊነፁ ከበደል ሊነፁ
ከዚያም የታጠቡ ኃጥአን
ከበደል ሊነፁ
2.
ያሟቹ ሌባ ደስ አለው
ያንን ምንጭ በማየት
እኔም እንደርሱ የበደልሁ
ከዚያ እነፃለሁ
ከዚያ እነፃለሁ ከዚያ እነፃለሁ
እኔም እንደርሱ የበደልሁ
ከዚያ እነፃለሁ
3.
አንተ የሞትህልኝ ጠቦት
የደምህ ኃይል አለው
የሚሞቱ ሰዎች ሁሉ
እስኪነጹ ድረስ
እስኪነጹ ድረስ እስኪነጹ ድረስ የሚሞቱ ሰዎች ሁሉ
እስኪነጹ ድረስ
4.
ያን ምንጭ ካየሁ በሃይማኖት
ያዳነኝን ከሞት
የገዛኝ ፍቅር ብቻ ነው
ነፍሴን የሚያረካው
ነፍሴን የሚያረካው ነፍሴን የሚያረካው
የገዛኝ ፍቅር ብቻ ነው
ነፍሴን የሚያረካው