1.
የጥንት አምባ የሱስ ነው
ስለኔ ተከፈለ
ወደ እርሱ ልሸሸግ
ከርሱ ጐን የወጣ ደም
ከኃጢዓቴ አጠራኝ
ስለዚህ ነው ያዳነኝ
2.
ሕግህን አልፈጸምሁም
አምላክ ሆይ በሥራዬ
ፍቅሬም የሞቀ ቢሆን
ሌትም ቀንም ባለቅስ
ሁሉ ሊያድን አይችልም
አንተ ብቻ አድነኝ
3.
የምሰጥህ የለኝም
መስቀልህን ብቻ አምናለሁ
አንተን ብቻ አመንሁኝ
ፀጋህ ብቻ ያድነኝ
ከኃጢዓቴ እጠበኝ
ያለዚያ እኔ ጠፊ ነኝ
4.
ሲያልፍ ሣል ይኸ ሕይወት
ዓይኔ ሲዘጋ በሞት
በዙፋንህ ፊት ለፍርድ
በምቀርብበቱ ቀን
አምባዬ ከመከራ
ባንተ ጥላ ሸሽገኝ