ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #193h / Song #193h

ሰንበትን አንርሣ

Don't Forget the Sabbath

ምድብ / Category: ሰንበት / Sabbath
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ሰንበትን አንርሣ የተባረከች ነች
ከቀን ሁሉ ያበራች በጣም የበለጠች
ዕረፍትን ታመጣለች ደስታን ትነግራለች
መለኮታዊ ብርሃን ታወርድልናለች
እንኳን ደህና ደህና መጣሽ
ብሩክ የሰንበት ቀን
እንኳን ደህና ደህና መጣሽ
ብሩክ የሰንበት ቀን
2.
ሰንበትን ቀድሱ ለእርሱም ስገዱ
ለተማሮቹ ብሏል እኔ ነኝ መንገዱ
በገርነት ብንሠራ ካምላክ ደስታ አለን
የዘለዓለም ብርሃን እንቀበላለን
3.
በደስታ ቅዱስ ቀን በምስጋና መዝሙር
ለወደደነ የሱስ ከልብ እንዘምር
ኦ ቸር መድኃኒታችን ስለኛ የሞትኸው
ተስፋህ ለልቦች ሁሉ የተከበረ ነው
100%
100%