ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #195h / Song #195h

የደስታ የዕረፍት ቀን

O Day of Rest and Gladness

ምድብ / Category: ሰንበት / Sabbath
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የደስታ የዕረፍት ቀን የደስታ ብርሃን ቀን
የኃዘን ማራቂያ በጣም የተዋበች
በዚያችም ቀን ለመስገድ
በዙፋን ፊት ቀርበን
እንዘምርም አለን ቅዱስ ቅዱስ ብለን
2.
አንች የታጠርሽ ወደብ
ሞገድ የማይነካሽ
ውቧ ያታክልት ቦታ
በመስኖ የረካሽ
ከምስጭው ውኃ
ጠጥተን እንረካለን
ባንቺ ላይ ቁመን ልናይ
የተስፋ አገራችን
3.
የመታሰቢያ ቀን
አንቺ የፍቅር ቀን
የሰማያዊን ደስታ
የምታሳስቢን
አዲሲቱንም ፀጋ
እንቀበላለን
የቀረውም በረከት
ከላይ ይቆየናል
100%
100%