1.
ልንሰማ እንሰብሰብ ቃልህን ጌታችን ሆይ
እንደ ዝናብ በድርቅ ምድር በልባችን እንዲቆይ
መንፈስ ቅዱስን ስጠን በልባችን አብራልነ
ችግረኞችን አጽናና ጌታ ሆይ በቃልህ
ችግረኞችን አጽናና ጌታ ሆይ በቃልህ
2.
ለመጠበቅ አስተምረን ነገሩን የሰጠኸን
በብርሃንህ አብራልነ በቅን መንገድም ምራን
ልቦናችንን አጽናና ከጥርጣሬ ጠብቀን
ጸጋህን አሁን ስጠነ ጌታ ሆይ በቃልህ
ጸጋህን አሁን ስጠነ ጌታ ሆይ በቃልህ
3.
የፀጋ ዘመን ልንጠብቅ እግዚአብሔር ሲፈልገን
ጊዜያችን እንዳናጠፋ ያለ ተስፋ እንዳንሆን
ስለዚህ አስታውቀነ ምሕረትህንም ስጠነ
ጆሮዋችንን ክፈትልን ጌታ ሆይ በቃልህ
ጆሮዋችንን ክፈትልን ጌታ ሆይ በቃልህ