ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #199h / Song #199h

መጽሐፉን ስጠኝ

Give Me the Bible

ምድብ / Category: የእግዚአብሔር ቃል / God's Word
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
መጽሐፉን ስጠኝ ብርሃን እንዲሆነኝ
በችግር ጊዜ ደስ እንዲያሰኘን
የሰላም ጮራን ማንም የማይጋርደኝ
የሱስ መጣልኝ እኔን ሊያድነኝ
መጽሐፉን ስጠኝ ብርሃን እንዲሆነኝ
በቀጭን መንገድ ብርሃንህ ይምራኝ
ሕግና ተስፋ ፍቅርና ደስታ
እስከ ዘላለም እንዲኖሩልኝ
2.
መጽሐፉን ስጠኝ ልቤ ሲሸበር ሳል
ኃጢዓት ኃዘንም ነፍሴን ሲያስቸግር
የከበረውን የአንተን ቃል ልማር
የሱስ መቅረቡን በእምነት ልመልከት
3.
መጽሐፉን ስጠኝ መንገዴ እንዲበራ ምድራዊ ተድላ እንዳያታለኝ
በጨለማ ውስጥ እንዲያበራልኝ
ቃልህ ነው መንገዱን የሚያሳየኝ
4.
መጽሐፉን ስጠኝ ያን የሕይወት መብራት
ከኃዘን ሥፍራ እርሱን አብራልኝ
የሰማያዊዩን ብርሃን አሳየኝ
ቃልህን እንዳስተውል አድርገኝ
100%
100%