ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #83t / Song #83t

በክቡር ደሙ ተዋጅተን

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
በክቡር ደሙ ተዋጅተን
የእጁ ብጐች የሆንን
ሥሙን ከፍ እያደረግን ጌታችንን እናምልከው
በደስታ እየዘመርን በዕልልታ እናንግሰው
1.
በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከን
ነውር የሌለበትን መስዕዋት አቅርበን
በእርሱ ባደረገ በፈጠረን
በአምላካችን እጅግ ደስ ይበለን (2x)
2.
ጌታ ስናመልከው ደስ ይለዋል
ስናመሰግነው ክብሩ ይጋርደናል
እህል ውኃችን ይባረካል
ለበሽታችንም ፈውስ ይሆናል (2x)
3.
ሩጫን አብዝተናል ያለመጠን
ነፍሳችን ደረቀች አምልኮ አስቅርተን
እንድንለመልም አቆጥቁጠን
ጌታንን እናምልከው አስቀድመን (2x)
100%
100%