ያይሃል ያይሃል ያይሃል ያይሃል
ያይሃል ኢየሱስ ያይሃል
ያይሃል በዕውነት ያይሃል
የአንተ ነገር ይገደዋል
ሊታደግህም ይመጣል
1.
በምድረ በዳ ያለኸው
እንደ አጋር ያነባኸው
የሚያይህንስ ብታየው
ፍጻሜህማ ተስፋ አለው
2.
ኑሮ ቢመሳቀልብህ
የያዝኸው ቢበተንብህ
ጌታም የተወህ ሲመስልህ
ጠላትህ ሲዘብትብህ
3.
ልብህ ሲያዝን ሲተክዝ
ለሕይወትህ ጽኑ ምርኩዝ
አይዞህ ባይ የሚያበረታ
ከቶ ማን አለ እንደ ጌታ?
4.
ሸክምን የሚያራግፍ ጌታ
የችግረኞች መከታ
ታማኝ የበጐች እረኛ
አማኑኤል አለን ለእኛ
5.
ሸክምን የሚያራግፍ ጌታ
የችግረኞች መከታ
ታማኝ የበጐች እረኛ
አማኑኤል አለን ለእኛ