ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #164t / Song #164t

የሰራልኝን ድንቅ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ
ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ
በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ (2x)
1.
በእለት እርምጃዬ እግሬን የሱስ ቀድሞ
ምህረቱን አብዝቶ ተዓምራቱን ደግሞ
አሳየኝ አምላኬ የከበረ ነገር
እንደዚህ ሊመራኝ ወደ ፃድቃን አገር (2x)
2.
በቀኝ በግራዬ አድፍጦ አድብቶ
መልካም መሰል አጥፊ ወጥመዱን ዘርግቶ
ጌታ ግን ሲያድነኝ በጦር ተደራጅቶ
ዲያብሎስ ሊያጠቃኝ
ነበር ተሰናድቶ (2x)
3.
እርሱ ቅጥር ሲቀጥር በእምላኬ እየዘለልኩ
ወጥመድ ሲዘረጋ እኔም እያመለጥኩ
በእኔ ብርታት ሳይሆን በጌታ እየታመንኩ
ሩጫ ቀጥላለሁ ሁሉን እያሸነፍኩ (2x)
4.
በዘለዓለም መድህን ከጥልቁ ወጥቼ
ከአባት ከእናት ዘመድ የሚበልጥ አግኝቼ
በአህዛብ መሃከል ለርሱ ዘምራለሁ
የከበረ ሥሙን አመሰግናለሁ (2x)
100%
100%