1.
አይሁድ ምልክት ይለምናሉ
ግሪኮች ጥበብ ይሻሉ
ጌታን ስተው ይቅበዘበዛሉ
እኛ ግን የሞተልንን
በደሙም የተቤዥንን
አዳኝነቱን ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ሁሉ እንሰብካለን
አዎን እንሰብካለን (2x)
2.
ያልገባቸው ቢያላግጡበትም
እንደ ሞኝነት ቢቆጥሩትም
በመስቀሉ ቃል አናፍርበትም
3.
የመዳኑን ፀጋ መጠራቱን
ከኃጢአን መሃል መውጣቱን
ባይቀበሉትም እንኳን ወንጌሉን
4.
እኛ ምልክታችን ኢየሱስ
ጠበባችንም ክርስቶስ
አለቃችን ነው የሰላም ንጉሥ
5.
ባዶ ተስፋ ፍፁም አናወራም
ከሥጋችን አንዘራም
ጌታችን አለና አንፈራም
6.
ለሚጠይቀን ሁሉ መልሳችን
የቀራንዮ ወዳጃችን
ኢየሱስ ጌታ ነው ስብከታችን