1.
የክሱን ክምችት የዕዳውን ጽህፈት
ደምስሰህልናል በመስቀልህ ምህረት
አንተ አጽድቀኸናል ማነው የሚከሰን
ከጸናችው እጅህ የለም የሚነጥቀን
ጌታ ሆይ ተመሥገን
አንተ የእውነት አምላክ እውነተኛ ዳኛ
ከከሳሽ ያዳንከን ፈርደህልን ለእኛ
ጌታ ከመንበርህ ከጽድቅ ዙፋንህ
መድኃኒትን ልከህ በአንተ አርፏል ሕዝብህ
2.
ተረታሁኝ ብሎ ጠላትም ባይተኛ
የማንተቀላፋ ጌታ አለህ ለእኛ
ደምፅህን ሲሰማ አጥማጅህ ገለል ይላል
ከመከራም ስጋት በአንተ ያመነ ያርፋል
ተከልሎ ይኖራል
3.
ከሳሻችን ወድቆ እኛ ተነስተናል
ጉልበታችን ፀንቶ እነሆ ቆመናል
ታዳጊያችን ሆይ ተመሥገን እንበልህ
ከአዳኙ ወጥመድ የወጣን ሕዝበህ
ማርኮናል ፍቅርህ