ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #133t / Song #133t

ተነሥ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ተነሥ (4x)
የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ
ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ (2x)
1.
ሕዝብህ በምድረ ግብፅ ኑሮ ቢመራቸው
ከበግ ጥበቃ ላይ ሙሴን የጠራኸው
የዘመናት ንጉሥ እግዚአብሔር ሆይ
ዘንዶውን የወጋህ አንተ አይደለህም ወይ
2.
የሳተም ይመለስ የዛለም ይበርታ
የኃጢአት ምርኮኛ ከእስራት ይፈታ
ክንድህን ስንጠብቅ በናፍቆት ዝለናል
እስኪ አንድ ጊዜ ጐብኘን ተጠምተናል
3.
ያለፉት ባሮችህ አስከብረውሃል
ኃይልህ ከላይ ሲወርድ ከአንበሳ ገጥመዋል
አንካሶች ሮጠዋል ጋኔሎች ወጥተዋል
ጊዜ እይለውጥህም እኛም አይተንሃል
100%
100%