1.
ወንድሞች በሕብረት ቢቀመጡ ቀርበው
ለማነጽ የሚጠቅም የፀጋ ቃል ይዘው
አፋቸውን ሲከፍቱ በክርስቲያን ቋንቋ
ምንኛ ደስ ይላል ሲቀር አሉባልታ
ሕይወት ለተጠማ የምሥራች በሉ
እንዲህ ያለ ኑሮ ወደው ቢቀበሉ
ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ይሰበካል
የሚያረካ ምንጭ ለሁሉም ተሰብኳል
2.
የመንፈስን ፍሬ አዝሎ በሕይወቱ
የአምላክን ደራሲ አውቆ ማንነቱን
ጌታን ሲያንፀባርቅ እስከ ዕለተ ሞቱ
ከክበር ወደ ክብር ይለወጣል ቤቱ
3.
ሸክምን ለማራገፍ በመስቀሉ እግር
ክርስቲያን ሲንበረከክ ልቡ ሲሰባበር
ሚስጥሩን ለጌታ በእንባ አወያይቶ
ተፅናንቶ ይነሳል በእምነት ተሞልቶ
4.
ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረቱ ጠንክሮ
ሕይወት ሲስተካከል ግንኙነት ሰምሮ
ኑሮ ከኢየሱስ ጋር ዓለምን ያስንቃል
ለዛ አለው ይጥማል ቢመረጥ ይበጃል