ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #91t / Song #91t

በወንጌል እውነት

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በወንጌል እውነት ወገቡን ታጥቆ
ስለ ሕይወት ቃል ጸንቶ ተዋድቆ
በጌታ ብርታት የከበበውን ጭፍራ ሰንጥቆ
በጐ ወታደር በድል አለፈ ያንን የሞትን ሸለቆ
1.
ለተጨነቀ ልቡ እረፍት አግኝቶ
ጉዞውን ቢጀምር ወደ ሰማያዊ አገር አቅንቶ
ሰይጣን በተንኮሉ በወጥመዱ አጥሮ መንገድ ቢዘጋበት
ጌታም ይህን አይቶ ወጥመዱን ሰባብሮ በሩን ከፈተለት
2.
መዋጋትን እንዲለምድ ሸለቆ ወርዶ
ከቤት ከንብረቱ ከነፍሱ አብልጦ ጌታውን ወዶ
ሰልፉ በረታና ክፉኛ ተጠቅቶ እጅና እግሩ ዝሎ
ኢየሱስ ደርሶለት ድልን አወጀለት ባላንጣውን ጥሎ
3.
እጆቹን በእርፉ ላይ አንዴ አሳርፏል
ወደኋላ ማየት ነውር በመሆኑ ሥራውን ቀጥሏል
እምነት ሳይጓደል አደራ ሳይበላሽ ተጠንቅቆ ታግሎ
እፎይ ማለቱ ነው በክብር ተራራ አክሊል ተቀብሎ
100%
100%