ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #93t / Song #93t

በድንገት ይመጣል

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የዓለም ፍጻሜ ምልክቶች
የጌታችን ቃሎች ትንቢቶቹ
ተፈፅመዋል የሚበዙቱ
የምጽአቱ ቀርቧል ሰዓቱ
ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ግርማ በድንገት ይመጣል
በሰማይ ደመና ከቅዱሳኑ ጋር በክብር ይገለጣል
ፊቱ ልትቆም ምን ያህል (2x) ተዘጋጅተሃል
2.
ረሃብ ቸነፈሩ የምድር መናወጥ
የአህዛብ ዕውቀት መከራና ምጥ
ፍጥረቱን ይዞ ሲያንገዳግደው
የጨለማው ገዥ ጨንቆ ሲያብሰው
3.
ሃሰት አሰራር ተዓምራቱ
የዓለም ሕዝቦችም ሲሳሳቱ
ዋጋ ሲያስከፍል ጌታን መጥራቱ
ቀኑም ቅርብ ነው የድል ንጋቱ
4.
ፍፁም ባላሰብከው ሰዓት ይመጣል
ነቅቶ መጠበቁ ይሻልሃል
በምቾት ወጥመድ እንዳትታለል
በጸሎት እየተጋህ ተጠንቀቅ
5.
ወንጌል ታውጆ የዘለዓለም
ሰዎች አምልጠው ከጥፋት ዓለም
የተባረከ ተስፋችን ኢየሱስ
ክፉን ደምስሶ በድል ሊነግስ
100%
100%