ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #130t / Song #130t

ከአምላካቸው በቀር

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ከአምላካቸው በቀር ማንንም እንዳያመልኩ
ለወርቁ ምስል እንዳይሰግዱ እንዳይንበረከኩ
ሰወነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን
ወዳጆቹን ያዳነ በእርሱ የታመኑትን
የሲድራቅ የሚሳቅ የአብድናጐም አምላክ
ለዘለዓለም ይባረክ
1.
እንደ እርሱ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና
ከእቶኑ እሳት ሊያድናቸው ችሏልና
ማዳን የእርሱ ነውና (2x)
2.
ጌታ ተናገረ እኔም ይህንን ብቻ ሰማሁ
ኃይል የእግዚአብሔር መሆኑን ተገነዘብሁ
እሳቱ ሲያጠፋ አየሁ (2x)
3.
ሰውነታችሁን ብትሰጡ ሳትሰስቱ
እግዚአብሔር ይሰራል አይፋጅም ከቶ እሳቱ
ሥሙን አስከብሩ በርቱ (2x)
100%
100%