ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #194t / Song #194t

የማይናወጥ መሰረቴ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የማይናወጥ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ መከታዬ
የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ
1.
በዚያ ሸለቆ በሀዘኑ ቦታ ኢየሱስ አልተውከኝም ደጋፊ እንዳላጣ ሕይወቴ ነህና ተድላ መከታዬ ኢየሱስ ከአንተ በቀር የቱ ነው ጋሻዬ
2.
የዓለሙ ወጀብ ሊመታኝ ሲቃጣ ጌታ አለቀቀኝም ከእጁ እንድወጣ ወደ እርሱ የመጡትን ልጆቹን ያፈቅራል በእቅፉ ውስጥ ይዞ ይጠብቃቸዋል
3.
የጣርህን መጠን በምን ልገምተው የውለታህን ልክ በምን ላስተውለው ከቶ እንዳልዘነጋው ያንን መስቀልህን ደግሞም እንዳልረሳ ለእኔ ማንባትህን
100%
100%