ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #117t / Song #117t

አዲስ ዝማሬ እንዘምር

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
አዲስ ዝማሬን እንዘምር
ለመድኃኒታችን ክብር
የምሥጋናችንን ሽታ
እናሳርግ በዕልልታ (2x)
1.
በእረኛቸው የታመኑ በመስኩ የተሰማሩ
ዱካውን እየተከተሉ ለደህንነት የተጠሩ
ከጨካኝ አውሬ የዳኑ ከመታረድ የተረፉ
ሃሴትን እንደሚያደርጉ በአጥፊው ጥፋት ስላልጠፉ
2.
ማቃችንን ቀዷልና ፀጋውን አልብሶናልና
ክብራችን ትዘምርለት ፍቅሩ አጽናንቶናልና
ጉዳታችንን የሚሹ ጉድጓድ ምሰው የጠበቁን
አጋንንት አፍረዋልና ያደፈጡት ሊያጠቁን
3.
በፍፁም ልብ እንዘምር በአምላካችን ደስ ይበለን
እናጨብጭብ ዕልል እንበል ለምንስ እንቆጥባለን
በምሥጋናችን ዝማሬ ምሽጉን እናፈርሳለን
በመንፈሳዊው ጦር ዕቃ ድል በድል እንሄዳለን
100%
100%