ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #136t / Song #136t

መልክህን ጌታዬ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
መልክህን ጌታዬ ጸሃይ አክስሎታል በሃሩሩ ብዛት ከስተህ ገርጥተሃል ምቾትም ድሎትም አልነበረህም ጌታ ለሰበዓዊው ፍጥረት በስቃይ ተመታህ (2x)
2.
የሞት ፅዋ ቀርባ ፈዋሼ ሲጨነቅ የአባቱ ድምፅ ርቆት በጭንቀት ሲሳቀቅ አንጀቱ ተጣብቆ አጥንቱ ሰልስሎ የእኔን ሕይወት ዋጀ ጌታዬ ተጋድሎ (2x)
3.
ተራራ እየቧጠጥክ በመዳህ ስትወጣ ሆንክልኝ መድህኔ ስለ እኔ ከርታታ ለአንተ የጣር ቀን ነው ለእኔ የፈውስ ዕለት ራስህን አጋልጠህ ፈፀምከው በትዕግሥት (2x)
100%
100%