ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #100t / Song #100t

ባለፍኩበት መንገድ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ማዕበሉ ፡ ሳይጥለኝ ፡ ውሃውም ፡ ሳያሰጥመኝ
እጄን ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ወንዙን ፡ አሻገረኝ
የፈተናው ፡ እሳት ፡ ወላፈን ፡ ሳይጎዳኝ
በጌታዬ ፡ ፀጋ ፡ በሕይወት ፡ አለፍኩት
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ
2.
ከሕያዋን ፡ ጋር ፡ ኖሬ ፡ እንዳከብርህ
ፈተናን ፡ አልፌ ፡ እንዳመሰግንህ
ኢየሱስ ፡ ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ አበረታኝ
ከአንበሳው ፡ አፍም ፡ ደጋግሞ ፡ አወጣኝ
3.
ሕይወቴን ፡ ለአምላኬ ፡ አደራ ፡ እየሰጠሁ
በእረኝነቱ ፡ ስር ፡ ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
በእርሱ ፡ ተጠብቄ ፡ ሃገሬ ፡ እገባለሁ
4.
ጌታ ፡ የሰራውን ፡ ድንቅ ፡ አስታውሳለሁ
ስላፈው ፡ ዘመን ፡ አመሰግናለሁ
ከፊቴ ፡ ላለውም ፡ በእርሱ ፡ እደገፋለሁ
በዘለዓለም ፡ ክንዱ ፡ በእቅፉ ፡ እኖራለሁ
100%
100%