ማደሪያዎችህ እንደ ምን የተወደዱ ናቸው
በቅዱስ ቃልህ በመንፈስህ የቀደስካቸው
ጌታዬ ሆይ! በመቅደስህ ከፍ ባለውም ዙፋንህ
ስግደት ይቅረብልህ ፤ ስግደት ይቅረብልህ
1.
ክቡር ድንጋዮች ሕያዋን ልጆች
በበጉ ደም የተዋጁ ሰዎች
ቤተ መቅደስ ለመሆን ታነጹ
ማደሪያ ሆኑለት ለንጉሡ
2.
በዓለም አዕላፍ ዕርካታን ያጡ
ዝናህን ሰምተው ከሩቅ የመጡ
በኃጥአን ድንኳን ከሚቀመጡ
በአንተ ማደሪያ መጣል መረጡ
3.
በጓዳዎችህ ክቡር ነገሮች
ተከምረዋል የሰማይ ሃብቶች
በመብራት በዘይትህም ቅባቶች
እጅግ ደመቁ የአንተ ልጆች
4.
ካህናቶችህ በመለከቶች
መዘምራን በዜማ ዕቃዎች
ባንድነት ቃና ወጣ ድምጻቸው
ከፍ አደረጉህ በምሥጋናቸው
5.
በዘለዓለማዊው ምሕረቱ
ልኡል ጐበኘን በቸርነቱ
ጌታ ለሕዝቡ ሰጠ ሞገሱን
የአምላኬ ክብር ሞላ መቅደሱን