ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #140t / Song #140t

የዘለዓለም አምላክ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
የዘለዓለም አምላክ የዘመናት ንጉሥ
ሁሉ በሁሉ ነው የናዝሬቱ ኢየሱስ (2x)
1.
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ኢየሱስ
አይሰለችም ከቶ አንተ እንኳን ብታምጽ
የመስቀሉ ቃል ፈውስ ነው ለሕይወት
አምነው ለተጠጉት ይሆናል መሰረት
2.
ለሰልፍ አዘጋጅቶ ኃይልን ያስታጥቃል
በላይ የቆሙትን ከበታች ይጥላል
በትንሳኤው ስልጣን ውጊያውን አካሂዶ
ምርኮን ሰብስብ አለው ጠላቱን አሳዶ
3.
ፍላጻን ወርውሮ ምሽግን ነደለ
በአምላኩ ተማምኖ ውጊያውን ቀጠለ
በደም ጐዳና ላይ የኢየሱስ ነው ድሉ
ብሎ ዘምሮለት ቆመ በዕጣ ክፍሉ
100%
100%