ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #170t / Song #170t

ጌታ ኢየሱስ አትተወኝ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
ኃጢአት በዛብኝ ጉልበቴም ደከመ
መራመድ አልቻልኩም መንገዴም ጨለመ
ጠላቴም ይህን ሲያይ ሊሰብረኝ አለመ
ጌታ ኢየሱስ አትተወኝ
አምላኬ ሆይ አትልቀቀኝ
በጭንቀት ታስሬ እያለሁ ዝም አትበለኝ
መጥተህ አውጣኝ
2.
አንተን እያሳዘንኩ ደምህን እየረገምኩ
ለልጆችህ ደግሞ እንቅፋት እየሆንኩ
መላው ጠፋኝ ጌታ ግራ ተጋባሁኝ
3.
ቃልህን እንዳላነብ ፍላጐቴ ከድቶኝ
ደግሞም እንዳልፀልይ ድካም ተጫጭኖኝ
በጣሙን ዝያለሁ ተጐሳቁያለሁ
4.
በቅዱስ መንፈስህ ሕይወቴ ታትሞ
በልጆችህ መሃል የእኔ መኖር ጠቅሞ
ልገናኝህ አብቃኝ ሁሉ ተፈጽሞ
5.
መውደቅ በጥቂቱ መሞት በጥቂቱ
መሆኑን አይቻለሁ ከመውደቅ ጠብቀኝ
ማዕበሉ እንዳይጥለኝ ጐርፉም እንዳይወስደኝ
100%
100%